About | ስለ

Purpose of Ethiopian Kale Heywot Church Link Organization

Welcome Message:

On behalf of the Kale Heywet Church in North America (KHCNA), I would like to say welcome to our website. This is one of the ways we connect and communicate with one another. The Bible in Hebrews 10:24-25 says that we need to consider to motivate one another for love and good works, and it encourages us not to neglect the assembling of ourselves together as we see the day of the Lord approaching.

The vision of seeing the Ethiopian Kale Heywet Church (EKHC) expanding its gospel ministry and influence outside Ethiopia was in the hearts and minds of the EKHC pioneer leaders for many years. This vision began to be seen in North America when EKHCLO was legally established in the United States in 2009. After four years, in 2013, EKHCLO organized the fellowship for KHC members who live in North America. In 2014, the first conference was held in Atlanta, GA. Since then, the conference continued annually for the fourth time in four different cities of the U.S.

God has repeatedly spoken in those conferences that we are sent by God to North America as messengers to share the gospel to all people and to plant churches. We are challenged that we have given much by God, and we have received the legacy from EKHC pioneer leaders to follow their example of proclaiming the gospel and planting churches wherever God put us. We should not imitate others to live a lifestyle of earthly comfort and safety for ourselves as people call it “The American dream;” instead, we are called to make a difference in the world in words and deeds.

Therefore, now is our time to shine the gospel. Let us pray together, encourage one another, and be engaged to fulfill the Great Commission of Jesus Christ in North America and beyond.

The Gospel Wins!

Rev. Terefe Anshebo (Dr.)
General Secretary of EKHCLO

 

 

 


“ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።” ዮሐ 9፡4 በሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ከርስቶስ ፀጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ለማለት እንወዳለን ።

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ከ1927 ዓ/ም ጀምሮ እግዚአብሔር በመከራውና በስደቱም ዘመን ሁሉ እየጠበቀንና በየዓመቱ እያሳደገን በአሁኑ ሰዓት ቁጥራችን ከ8 ሚልዮን ምዕመናንና ከ8 ሺህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በላይ ደርሶአል። ይህም ሊሆን የቻለው አባቶቻችን ለእግዚአብሔርና ለሰዎች ከነበራቸው እውነተኛ ፍቅርና፤ለወንጌል ሥራ ከነበራቸው ትጋትና ብርቱ ተጋድሎ መሆኑ ከማናችንም የተሠወረ አይደለም። እነዝያ ቀደምት የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች አብዛኞቹ አገልግሎታቸውን በክብር ፈጽመውና በዘመናቸው የእግዚአብሔርን ሀሳብ አገልግለው ወደሚወዱት አምላካቸው ተሰብስበዋል። ዛሬ ደግሞ አነርሱ ያስተላለፉልንን የወንጌል አደራ ተቀብለንና የነርሱን ፈለግ ተከትለን ጌታን ለማገልገል መሮጥ የኛ ድርሻና ዘመን ሆኖአል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በውጭ አገር በተለይም በሰሜን አሜሪካ የምንኖረውን የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አባላት በማሰባሰብ ሕብረት እንዲኖረን በማሰብ እ.አ.አ. ነሐሴ 10 ቀን 2013 በግራንድ ራፒድስ ምሽገን በተደረገ ው ስብሰባ “የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አባላት ህብረት በሰሜን አሜሪካ” በሚል ስም ተቅዋቁሞአል። ይህ ሕብረት ከአሜሪካን ፌዴራል መንግሥት ትርፋማ ያልሆነ (non-profit ) ከታክስ ነጻ የሆነ ህጋዊ እውቅና ባገኘው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ ሊንክ ኦርጋናይዜሽን (EKHCLO) ሥር ሆኖ የሚሠራ ነው። የሕብረቱ ሶስት ዋና ዋና ዓላማዎች 1) ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለማድረስ በያለንበት የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት እንድንችል ለማገዝ (ማቴ 28፡19-20)፤ 2) የቃለ ሕይወት ቤ/ክ አባላት እርስ በርስ ለመገናኘትና ለመደጋገፍ (ዕብ 10፡25)፤ 3) በተቀናጀ መልክ እናት ቤተ ክርስቲያናችን በምታደርገው የወንጌል ተጋድሎ በምንችለው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ነው (ዕብ 13፤6).

አቶ አሰፋ አይዛ የEKHCMFNA ቦርድ ሊቀመንበር

አቶ ተረፈ አንሼቦ የ EKHCMFNA ቦርድ ዋና ፀሐፊ

አቶ ብርሃኑ ደረሰ የEKHCLO ቦርድ ሊቀመንበር እና የEKHCMFNA አማካሪ